በኢንስቲትዩቱ በምርምር አፃፃፍ እና ህትመት ዙሪያ የአቅም ማጎልበቻ ሴሚናር ተካሄደ።

በኢንስቲትዩቱ በምርምር አፃፃፍ እና ህትመት ዙሪያ የአቅም ማጎልበቻ ሴሚናር ተካሄደ።

በኢንስቲትዩቱ በምርምር አፃፃፍ እና ህትመት ዙሪያ የአቅም ማጎልበቻ ሴሚናር ተካሄደ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አቅም ግንባታና ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት አቅም ግንባታ ዘርፍ አዘጋጅነት "በምርምር ጽሑፍ አዘገጃጀትና ህትመት" ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ሴሚናር ተካሂዷል።

ሴሚናሩ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ተመራማሪዎች፣ ከባለድርሻ ተቋማት እና አጋር ድርጅቶች ተወካዮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ነው የተካሄደው።

ሴሚናሩ ለፖሊስ ጥናት ፋይዳ ያለውን የምርምር አፃፃፍና ህትመት ዙሪያ ለተሳታፊዎች እውቀትን ለማጋራት፣ የምርምር ክህሎታቸውን ለማጠናከር እንዲሁም አቅም ለማጎልበት ያለመ ነው ተብሏል። 

በመርኃ ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አቅም ግንባታና ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር / ታከለ ታደሰ ሴሚናሩ በሳይንሳዊ ጥናት ያሉ ክፍተቶችን በመሙላት እና የተመራማሪነት አቅምን በማሳደግ ረገድ ጉልህ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።


የምርምር ህትመት ወረቀቶችን (Manuscripts) በማዘጋጀት በዓለም አቀፍ የምርምር መጽሔቶች (Journals) የማሳተም አቅማቸውን ለማሳደግ ሴሚናሩ በዋናነት ያለመ መሆኑን ፕሮፌሰር ታከለ በገለጻው ላይ ተናግረዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም፦ እንደ ተቋም በተናጠል እንዲሁም ከአጋር እና ባለድርሻ ድርጅቶች ጋር በትብብር የሚሰሩና ለፖሊሲ ግብዓትነት የሚውሉ የጥናትና ምርምር ሥራዎች ክፍተቶችን በመሙላት አንጻር ክልላዊና ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸውን ስራዎች በጥራት ማከናወን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የምርምር ስራዎች የማሕበረሰቡን ችግር የሚፈቱ፤ እንዲሁም አገር አቀፍ የልማት አጀንዳዎችን እና የትኩረት አቅጣጫ የሚያስቀድሙ ጭብጥ ተኮር  ስራዎች በማበርከት ለህትመት ማብቃት ተገቢ መሆኑንም አመላክተዋል።

ችግር ፈቺ ምርምር ማካሄድ ከኢንስቲትዩቱ ዋነኛ ተልዕኮ አንዱ መሆኑን / ታከለ ጠቅሰው፣ ተቋሙ የማህበረሰቡን ጉልህ ችግሮች በሳይንሳዊ መንገድ ለመፍታት የሚያግዙ የተለያዩ የምርምር ሥራዎችን ሲያከናውን መቆየቱንም አሳውቀዋል።

በቀጣይ ጊዜያት በኢንስቲትዩቱ የሚካሄዱ ጥናት እና ምርምሮች የማህበረሰቡን፣ የኢንዱስትሪውን እና የሀገራዊ የልማት ችግሮችን በቀጥታ የሚፈቱ እና ለሁለንተናዊ ሳይንስ እድገት አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ እንዲሆኑ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

በቀጣይ ጊዜ መሰል ሴሚናር በማዘጋጀት ምሁራን አቅማቸውን የሚገነቡበት አመቺ መንገድ እንደሚፈጠርና በቡድን የመስራት፣ የመደጋገፍና የመረዳዳት ባህላቸውን አሻሽለው ምርምሮችን በጋራ መስራት እና ውጤታማ መሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።

በኢንስቲትዩቱ የአቅም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ታምራት አሰፋ በበኩላቸው እንደ ተቋም ይህ የሴሚናር መድረክ የምርምር ጽሑፍ ዝግጅት እና የሕትመት ጥራትን ለማሳደግ፣ ተመራማሪዎች መካከል የእውቀት ልውውጥን ለማጠናከር እና በማህበረሰብ ላይ ተግባራዊ ተጽዕኖ ያላቸውን ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮች በጥራት እንዲካሄድ ከፍተኛ አቅም የሚፈጥር መሆኑን አመላክተዋል።


አቶ ታምራት አክለው በአቅም ግንባታ ዘርፍ የተመራማሪዎችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ በማጠናከር እና ቀጣይነት ባለው መልኩ ተቀናጅቶ በመስራት አዎንታዊ ለውጥ ለማምጣት እንዲቻል በትብብር ለመስራት ዕቅድ ተይዟል ብለዋል።

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፦ ምሁራኖች በትምህርት ዓለም የተገኘን ዕውቀት እንዲሁም ክህሎትን ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ ጋር በማዋሃድ የማኅበረሰቡን የኑሮ ሁኔታ የሚያሻሽሉ የተለያዩ ጥናትና ምርምሮች  በመሥራት አቅማቸውን እና እውቀታቸውን ማዳበር እንደሚገባቸው ገልፀዋል፡፡

የመድረኩ ተሳታፊዎች በሴሚናሩ የተሰጣቸውን የምርምር ጽሑፍ ዝግጅት እና ህትመት ስልጠና  ተግባር ላይ በማዋል ውጤታማ ተማራማሪዎች ሊሆኑ እንደሚገባ አቶ ታምራት አሳስበዋል። ይህ ሴሚናር በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድ ያደረጉ አካላትን እንዲሁም ተሳታፊዎችን አመስግነዋል።


በኢንስቲትዩቱ መሪ ተመራማሪ / ኦንጋዬ ኦዳ፦ ውጤታማ የምርምር ጽሑፍ አዘገጃጀት እና ህትመት በተመለከተ ባቀረቡት ገለጻ የምርምር ጽንስ-ሃስብ እንደ ተፈላጊ ዓውድ በሁሉም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚሰጥ ቢሆንም በዋናነት የማሕበረሰቡ ችግር ለመፍታት በሚያግዝ መንገድ ተግባር ላይ እንዲውል በማድረግ በኩል ግን የሚታይ ክፍተት እንዳለ ጠቅሰዋል።

በምርምር የተገኘ እውቀት የዘመኑን ቴክኖሎጂ በሚዋጅ እና የአከባቢውን ሃብት ጥቅም ላይ እንዲውል በሚያደርግ መንገድ የማሕበረሰቡን ችግር ለመፍታት እና ኑሮውን እንዲሻሻል ለማድርገ እንዲሁም ስታንዳርድ የጠበቀ የምርምር ጽሑፍ ለማዘጋጀትና ለህትመት ለማብቃት በማሰብ ይህ ይህ መድረክ መዘጋጀቱን አሳውቀዋል።

የዚህ ሴሚናር ዓላማ የምርምር ጥራትን ማሻሻል፣ ምሁራን የሚያዘጋጇቸው ትልመ ጥናቶች ጭብጥ ተኮር ሆነው ከሀገሪቱና ከክልሉ የትኩረት መስኮች ጋር እንዲሰናሰሉ ለማስቻል እንዲሁም የምርምር አፃፃፍ አቅምን በማጎልበት የምርምር ሪፖርት/ አርቲክል አፃፃፍ እና የምርምር ህትመት ጥራት በማሻሻል ለሀገራችን ፋይዳ በሚኖራቸው ደረጃ እንዲከናወኑ ለማስቻል መሆኑንም / ኦንጋዬ ጠቁመዋል።

ውጤታማ እንዲሁም ተወዳዳሪ የጥናትና ምርምር ጽሑፎችን ለመፃፍ ተጨማሪ አቅም ለመፍጠር ጥልቀት እና ስፋት ያለው ትምህርት የወሰድንበት ነው በማለት የሴሚናሩ ተሳታፊዎች ሀሳባቸውን ሰጥተዋል፡፡


በሴሚናሩ ላይ ገለጻ ያደረጉትን የኢንስቲትዩቱን ዋና ዳይሬክተር / ታከለ ታደሰን እና በተቋሙ መሪ ተመራማሪ የሆኑትን / ኦንጋዬ ኦዳ ተሳታፊዎች አመስግነዋል።

ኢንስቲትዩቱ በቀጣይነት መሰል የስልጠና ሴሚናር በማዘጋጀት የተመራማሪዎችን አቅም ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆኑን በማሳወቅ ውጤታማ የምርምር አፃፃፍ እና ህትመት በተመለከተ የተዘጋጀው አቅም ማጎልበቻ ስልጠና እንዲጠናቀቅ ተደርጓል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት አቅም ግንባታና ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት

ይህንን ዜና ያጋሩ